የጤና ጣቢያዉ ኃላፊ መልእክት

ውድ ተገልጋዮቻችን ጤና ጣቢያችን በወረዳችን የእያንዳንዱን ግለሰብ ጤና እና ደህንነት ለማሻሻል ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነው። የህዝብ ጤና ጥበቃ ስርዓት አስተዳዳሪ እንደመሆናችን በወረዳችን እያንዳንዱ ነዋሪ ፍትሃዊ፣ አካታች እና ዘላቂነት ያለው የጤና አጠባበቅ አገልግሎት እንዲያገኝ ያለመታከት እንሰራለን። ጤና በግለሰብ፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች እድገት ውስጥ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና እንገነዘባለን።

ባለፉት ጥቂት አመታት የወረዳችን የጤና ስርዓት ከፍተኛ እድገት አሳይቷል። የጤና እንክብካቤ መሠረተ ልማቶችን አሳድገናል፣ የሰው ኃይል አቅምን አስፋፍተናል፣ እና የአገልግሎት አሰጣጡን አጠናክረን እየጨመረ የመጣውን የህዝባችንን የጤና ፍላጎት ለማሟላት ችለናል። የሥራችን ቁልፍ ገጽታ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን ማሻሻልን ያካትታል። በወረዳዉ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ግለሰብ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን እንዲያገኝ ማድረግ ተልእኳችን እየተወጣን እንገኛለን። በጤና ጣቢያችን የእናቶች እና የህፃናት ጤና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። የሰለጠነ የወሊድ አገልግሎትን በማስፋት፣የቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ እንክብካቤን በማሻሻል እንገኛለን።

ፋንቱ እሸቱ , በልደታ ክ/ከተማ የአብነት ጤና ጣቢያ ኃላፊ
image description